ከህወሓት ጋር በትግራይ የሚካሄድ ጦርነት እንደሌለ የጠ/ሚ/ር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ

ከህወሓት ጋር በትግራይ የሚካሄድ ጦርነት እንደሌለ የጠ/ሚ/ር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የህወሓት ኃይል በከፍተኛ ደረጃ መሸነፉንና ተበታትኖ ባለበት ሁኔታ የተራዘመ የሽምቅ ውጊያ ማድረግ በሚችልበት አቋም ላይ እንደማይገኝ አስታወቀ።

መቀለ ከሳምንት በፊት ሰላማዊ ሰዎች ሳይጎዱና ንብርት ሳይወድም፣ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር ከገባች በኋላ ወታደራዊ ዘመቻው ተጠናቋል በማለት በትግራይ እየተካሄደ ያለው ሕግን የማስከበር ዘመቻ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ መግለጫ ያወጣው የጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት፤ የፌደራል መንግሥት በአሁኑ ተልዕኮው እየፈጸመ ያለው በሕግ የሚፈለጉ የህወሓት አመራሮችን ይዞ ለሕግ ማቅረብ፣ ሕግና ሥርዓትን ማረጋገጥ ብቻ ነው ብሏል።
ከዚህ ወሳኝ ጉዳይ ባሻገር በግጭት ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች የሰብኣዊ እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ፣ ግጭቱን በመሸሽ ወደ ጎረቤት ሀገራት የተሰደዱትን ወደ ቀያቸው መመለስ፣ የትራንስፖርት እና የግነኙነት መስመሮችን ጠግኖ ሥራ ማስጀመርንም መንግሥት በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተገበረ እንደሚገኝ መግለጫው ጠቁሟል።

LEAVE A REPLY