ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በዓለም ዐቀፉ የሥራ ፈጠራ ድርጅት የተዘጋጀና ለስደተኞች ሁለገብ መረጃ የሚያቀርብ የጉዞ ስንቅ የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ።
የሥራ አጥ ቁጥርን ከመቀነስ አንጻር መንግሥት በተለያዩ ዘርፎች የሥራ እድል ፈጠራ ላይ እየሠራ እንደመሆኑ አዲሱ የሞባይል መተግበሪያ ለስደተኞች የተሟላ መረጃ በመስጠት የዜጎችን እንግልት የሚቀንስ ነው ተብሎለታል።
የሞባይል መተግበሪያው ከስደት ሕይወት ጋር በተገናኘ የሥራ ዕድል አማራጮችን፣ የየአገራት ህግጋትንና የሚደርሱ ችግሮችን በዘርፉ ከሚሰሩ ተቋማት እና ኢምባሲዎች ጭምር በማስተሳሰር መረጃዎችን ጥቆማ ይሰጣል ተብሎለታል።