ብሔራዊ ባንክ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች የሚመዘገቡበት ዘመናዊ ኤሌክትሮኒክ ማዕከል አቋቋመ

ብሔራዊ ባንክ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች የሚመዘገቡበት ዘመናዊ ኤሌክትሮኒክ ማዕከል አቋቋመ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች የሚመዘገቡበት ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክ ማዕከል እንዳቋቋመ ገለጸ።

የባንኩ የፋይናሻል ኢንክሉዢን ዳይሬክተር ተመስገን ዘለቀ ተንቃሳቃሽ ንብረቶች የሚመዘገቡበት ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ማዕከሉ  ወደሥራ መግባቱን አረጋግጠዋል።
በልዮ ሁኔታ የተደራጀው ተንቀሳቃሽ ንብረቶች የሚመዘገቡበት ማዕከል ከባንኮች ብድር ለመውሰድ የሚፈልጉ ደንበኞች ያሏቸውን ተንቀሳቃሽ ንብረቶች በማስመዝገብ እና የተለየ መለያ ቁጥር፣ ወይንም ኮድ ለንብረቱ ከተሰጠ በኋላ ባለንብረቶቹ ለመበደር ወደ መደበኛ ባንኮች እና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ሲሄዱ የተመዘገበበትን ቁጥር ብቻ በመያዝ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል ነው ተብሎለታል።

LEAVE A REPLY