ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከተሽከርካሪ ምርመራና ብቃት ማረጋገጫ ሰርቸፍኬት አሰጣጥ አገልግሎት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው አራት ክልሎች የሥራ ጥራት ችግር በግልጽ ይታይባቸዋል ተባለ።
አደረግኹት ያለውን ጥናት ተከትሎ የትራንስፖርት ሚኒስቴር በአራት ክልሎች እና አንድ የከተማ አስተዳደር በተሸከርካሪ ምርመራ ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ተቋማት የሥራ ጥራት ችግር ያለባቸው መሆኑንና በትክክል ያልተረጋገጠ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እየሰጡ መሆናቸውን ገልጿል።
በኢትዮጵያ 95 በመቶ የሚሆነው የተሽከርካሪ ምርመራ የሚያደርጉ ተቋማት አዲስ አበባ ፣ ኦሮሚያ ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሶች እና ሕዝቦች ፣ ትግራይ እና አማራ ክልል የሚገኙ ሲሆን ፤ 41 በሚሆኑ የተሽከርካሪ ምርመራ በሚያካሂዱ ተቋማት ላይ በትራንስፖርት ሚኒስቴር በተደረገው ጥናት መሠረት አራት ክልሎችና አንድ ከተማ አስተዳደር በአግባቡ ምርመራ እንደማያደርጉ ተረጋግጧል።