አንቶኒዮ ጉተሬዝ በትግራይ ክልል ባለው ሁኔታ ለኢትዮጵያ መንግሥት ማሰጠንቀቂያ ሰጡ

አንቶኒዮ ጉተሬዝ በትግራይ ክልል ባለው ሁኔታ ለኢትዮጵያ መንግሥት ማሰጠንቀቂያ ሰጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ክልል የሕግ የበላይነትን በአፋጣኝ መመለስ ተገቢ ነው ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ መንግሥትን አሳሰበ።

“የሰብአዊ መብቶችን ባከበረ ሁኔታ በአፋጣኝ የሕግ የበላይነትን በፍጥነት መመለስ ያስፈልጋል” ያሉት የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፤ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በእጅጉ እንዳሳሰባቸውም ገልጸዋል።
ጥቂት የማይባሉ ሰዎች በትግራይ ክልል ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ነጻ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር እንዲመቻችም ዋና ጸሐፊው ጠይቀዋል።
ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ለእርዳታ አቅርቦት ሠራተኞች የሚያገለግል መተላለፊያ መስመር እንደሚከፍቱ አስታውቀው ነበር።

LEAVE A REPLY