በትግራይ ባሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች ላይ መተኮሱንና መያዙን የኢትዮጵያ መንግሥት አመነ

በትግራይ ባሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች ላይ መተኮሱንና መያዙን የኢትዮጵያ መንግሥት አመነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ክልል የፍተሻ ቦታ በጣሱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች ላይ ተኩስ መከፈቱንና ሠራተኞቹ መያዛቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አመነ።

የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞች ባለፈው ሳምንት እሁድ ኅዳር 27/2013 ዓ.ም የኤርትራ ስደተኞች የሚገኙበትን ማዕከልን ለመጎብኘት ሲያቀኑ የፍተሻ ጣቢያዎቹን ጥሰው እንዳለፉ ተገልጿል።
የድርጅቱ ሠራተኞች መሄድ ወዳልተፈቀደላቸው አካባቢ በመግባት የመንግሥትን መመሪያ በመተለለፋቸው ሊተኮስባቸውና ሊያዙ መቻላቸውን የጠቆሙት አቶ ሬድዋን ሁሴን፤ ” ሠራተኞቹ ሁለት የፍተሻ ጣቢያዎችን በመጣስ ነድተው ነው ያልተፈቀደላቸው ቦታ የገቡት፤ እንዳይሄዱም ተነግሯቸዋል። ሦስተኛውን የፍተሻ ጣቢያም ሊጥሱ ሲሉ ነው ተተኩሰባቸው በቁጥጥር እንዲው የተደረጉት” በማለት ሂደቱን አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY