ዐቢይ አሕመድና ኡሁሩ ኬንያታ የሀዋሳ ሞያሌ መንገድና የጋራ ፍተሻ ጣቢያ መርቀው ከፈቱ

ዐቢይ አሕመድና ኡሁሩ ኬንያታ የሀዋሳ ሞያሌ መንገድና የጋራ ፍተሻ ጣቢያ መርቀው ከፈቱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና  የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አገራቱን የሚያስተሳስረውን የሞምባሳ-ናይሮቢ -አዲስ አበባ ኮሪደር ግንባታ አካል የሆነውን የሀዋሳ-ሞያሌ መንገድና የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ መርቀው ከፍተዋል።

አዲሱ መንገድ ከሀዋሳ ከተማ እስከ ኬንያዋ አሲአላ ከተማ 1 ሺህ 3 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ አለው።
የመንገዱ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆን የሁለቱን ሀገራት ሕዝቦች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የትራንስፖርት አገልግሎትን የተሳለጠ በማድረጉ ረገድም ድርሻው የጎላ ነው ብለዋል።
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ከምረቃ ሥነ ሥርዓቱ በኋላ በሞያሌ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎችን ያነጋገሩ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሁለት ቀናት በኬንያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY