ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በሦስት ተጨማሪ ቋንቋዎች ሥርጭት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።
የአማራ ክልል ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ባስገነባው ስቱዲዮ ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ በትግረኛ፣በኦሮምኛ እና በአረብኛ ቋንቋዎች ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑንም እወቁልኝ ብሏል።
የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሙሉቀን በሦስቱ ቋንቋዎች ፕሮግራም እንደሚጀምር ከመግለጻቸው ውጪ ስለዝግጅቶቹ ይዘትና የሰዐት መጠን ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም።