ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከህወሓት ጽንፈኛ ቡድን ጋር በት የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ መጠነ ሰፊ የመረጃ መረብ ጥቃትና አገልግሎት የማስተጓጎል ሙከራዎችን ማምከኑን ኢትዮ ቴሌኮም ገለጸ።
በትግራይ መደበኛ የቴሌኮም አገለግሎት ከመቋረጡ ባሻገር በመንግሥት የኮምፒውተር ሥርዓቶችና ድረ ገጾች ላይ፣ በትምህርት፣ በፋይናንስ፣ በመገናኛ ብዙሃን እንዲሁም በቴሌኮም መሰረተ ልማቶችና ሲስተሞች ላይ መጠነ ሠፊ የመረጃ መረብ ጥቃት ሙከራ መደረጉን ተሰምቷል።
በመቀለና ሽረ የሚገኙት ዋነኛ ማዕከላት ላይ የአገልግሎት መቋረጥ ከማጋጠሙ በፊት ችግር ሊያስከትል የሚችል ምንም አይነት መረጃ እንዳልነበረ፣ የኃይል መቋረጥ ካጋጠመመም በማዕከላቱ ያሉትም ጄኔሬተሮች ምንም ችግር እንዳልነበረባቸው ያስታወሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ሆን ተብሎ ኃይል እንዲቋረጥ መደረጉንም አረጋግጠዋል።
በትግራይ ወታደራዊ ግጭት በተከሰተበት ዕለት ከድርጅቱ ሠራተኞች ውጪ የሆኑ አካላት በሰሜን ሪጂን ውስጥ ወደሚገኙት የመቀለ እና የሽረ ዋነኛ ጣቢያዎች በመግባት አገልግሎት የማቋረጥ ድርጊት መፈጸማቸውን ከደኅንነት ካሜራዎች ላይ መታየት መቻሉ ታውቋል።