ኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ቫይረስ ነፃ ምርመራ መጀመሯን አስታወቀች

ኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ቫይረስ ነፃ ምርመራ መጀመሯን አስታወቀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትዮጵያው የኮቪድ 19  ነፃ ምርመራ ማድረግ መጀመሯን የጤና ሚኒስቴር እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጹ።

በመሆኑም ዜጎች በአዲስ አበባ በሚገኙ በተመረጡ 34 የጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች ከክፍያ ነፃ ናሙና በመስጠትም ምርመራ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።
ምኒልክ ሆስፒታል፣ አቤት ሆስፒታል፣እንጦጦ ፋና የጤና ማዕከል፣ ህዳሴ የጤና ማዕከል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ የካቲት 12 ሆስፒታል፣ የነፃ ምርመራ ይካሄድባቸዋል ከተባሉት ሆስፒታሎች ውስጥ ለአብነት ተጠቃሽ ናቸው።
በመዲናዋ  ባሉ የጤና ተቋማት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ለማድረግ 1 ሺኀ 250 ብር ክፍያ በአማካይ ሲያስከፍሉ መቆየታቸው ታውቋል። መንግሥት ቀደም ሲል ከቫይረሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ብቻ ሲመረምር መቆየቱ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY