ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በጁንታው ጦርና በሀገር መከላከያ ሠራዊት መሀል የተካሃደውን ጦርነት ተከትሎ በዳንሻ፣ ኮረም፣ ሁመራና ማይጨው በከፊል የቴሌኮም አገልግሎት ተጀምሯል ተባለ።
ኢትዮ ቴሌኮም ትግራይ ክልል ላይ በነበረው ህግን የማስከበር ሥራ ላይ ስለተቋረጠው የቴሌኮም አገልግሎት ዛሬ ይፋዊ መግለጫ ሰጥቷል።
እንደመግለጫው ከሆነ በዳንሻ፣ ኮረም፣ ሁመራና ማይጨው የቴሌኮም አገልግሎት በከፊል ሥራውን የጀመረ ሲሆን በአላማጣ ደግሞ ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱ መሰጠት መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል።