ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፎርብስ መጽሔት ባወጣው የዓመቱ (2020) 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ተሰማ።
96ኛ ደረጃ የተቀመጡት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዝርዝሩ የተካተቱ ብቸኛዋ አፍሪካዊ ሴት ሆነዋል።
ፕሬዝዳንቷ ለምክር ቤት ባደረጉት የመጀሪያ ንግግር ለሴቶች ድምፅ ለመሆን ቃል ገብተዋል በማለት የገለጻቸው ፎርብስ መጽሔት፤ የፕሬዚዳንቷ መመረጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጠኑም ቢሆን የሴቶች ውክልና እየጨመረ መምጣቱን አመላካች ነው ብሏል።
አንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት የጀርመኗ መራሔተ መንግሥት አንጌላ መርክል ሲሆኑ፤ መርክል በዝርዝሩ ለዐሥር ተከታታይ ዓመታት መሪነቱን ይዘው ከመቀጠላቸው ባሻገር በዝርዝሩ ውስጥ ለአስራ አምስት ዓመታት መካተት ችለዋል።