ለማትሪክ ተፈታኞች ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለመከለስ የሚያስችል የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተዘጋጀ

ለማትሪክ ተፈታኞች ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለመከለስ የሚያስችል የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተዘጋጀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፈው አመት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሳይፈተኑ ለቀሩትና በቅርቡ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለመከለስ የሚያስችል የቴሌቪዥን ፕሮግራም እንደተዘጋጀ ተሰማ፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር ቴሌቪዥን የሚሰራጨው ፕሮግራም ሠባት የትምህርት ዓይነቶችን ማለትም እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስን ያካተተ ነው።
የፈተና ጊዜው ከመቃረቡ አኳያ የትምህርት ፕሮግራሙ ከሰኞ እስከ እሁድ በድግግሞሽ እንደሚተላለፍ የጠቆመው ትምህርት ሚኒስቴር፤ ወላጆች ለልጆቻቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ከወዲሁ ምክር ለግሷል።

LEAVE A REPLY