ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የሀገር መከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላትን በማሳገት የተጠረጠሩ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የሀገር መከላከያና የፖሊስ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱ ታወቀ።
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ የተካሄደውን አሳፋሪ የእገታ ተግባር እንደመሩና እንዳስተባበሩ በምርመራ የተደረሰባቸው 40 የከዱና በጡረታ የተገለሉ የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የሀገር መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ዛሬ ይፋ ተደርጓል።
የእስር መያዣው ከወጣባቸው መካከል ሜጀር ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ፣ ፡ኮሎኔል በርሄ ወልደ ሚካኤል ገብሩ፣ ኮሚሽነር ይህደጎ ስዩም ወልደማርያም ይገኙበታል።