ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያን በዓለም አትሌቲክስ ዘርፍ በማስተዋወቅ ረገድ ግንባር ቀደም የሆነው የሻምበል አበበ ቢቂላ የሮም ኦሎምፒክ 60ኛ ዓመት የማራቶን ድል የዘከረ ፕሮግራም ተካሄደ።
በዝክር ፕሮግራሙ ከአበበ ቢቂላ ባሻገር ከሜልቦርን (1956) እስከ ሪዮ ዲ ጄኔሮ (2016) ኦሎምፒክ ጨዋታዎች በአትሌቲክስ ተሳትፈው ሀገር ያኮሩ ጀግኖችም ታውሰውበታል።
በፕሮግራሙ ላይ የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሣው፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር፣ የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ ጨምሮ የፕሮግራሙ አካል የሆኑ የኦሎምፒክ ጀግኖች እና ታዋቂ አትሌቶችና ቤተሰቦቻቸው ተገኝተዋል።