መከላከያ ሠራዊቱ ወንጀለኞችን የማደን ሥራውን አጠናቆ በቅርቡ ወደ መደበኛ ሥራው ይመለሳል ተባለ

መከላከያ ሠራዊቱ ወንጀለኞችን የማደን ሥራውን አጠናቆ በቅርቡ ወደ መደበኛ ሥራው ይመለሳል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– መከላከያ ሠራዊቱ ወንጀለኞችን ለሕግ የማቅረብና ሌሎች ግዳጆችን አጠናቆ በቅርቡ ወደ መደበኛ ሥራው ይመለሳል ተባለ።

ጁንታው የአብራኩ ክፋይ የሆኑ የሠራዊት አባላትን የበላ አሸባሪ ኃይል ነው ያሉት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ብርሃኑ ጁላ፤ ጦርነቱ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ያልቃል ብሎ የገመተ ባይኖርም  ሀቅና ፍትህ ስላለን በአጭር ጊኤ ጁንታውን ላይመለስ መደምሰስ ተችሏል ብለዋል።
የትግራይና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተገላግሏል ያሉት ኢታማዦር ሹሙ፤ መከላከያ ሠራዊቱ በአሁኑ ወቅት የመንግስትን የመልሶ ማቋቋም ስራ የመደገፍና መደበኛ የፖሊስና የትራፊክ አገልግሎቶች እንዲስተካከሉ የማገዝ ሥራ እየከወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY