ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በትግራይ ክልል የጭላ ወረዳ ጁንታው ደብቋቸው የነበሩ ከ140 በላይ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ ፈንጂዎችን ጨምሮ በርካታ የከባድ መሳሪያ ተተኳሾች ተያዙ።
ጁንታው የመከላከያ ሠራዊት አይደርስበትም ብሎ በገመተው የጭላ ወረዳ ልዩ ስፍራው “ሰረፍረፍ” በተባለ አካባቢ ስንቅና ትጥቅ የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎችን ደብቋቸው ቢያስቀምጥም በአሰሳ መያዙን የ11ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ብርጌድ አዛዥ ኮለኔል ያሲን ኑሪዬ ገልጸዋል።
አካባቢው ከትህነግ አባላት ሙሉ ሙሉ ነፃ በመውጣቱ ሕብረተሰቡ ወደቀደመ የተረጋጋ ሕይወቱ እየተመለሰ እንደሚገኝና ሠራዊቱ የሕብረተሰቡን ሰላም ከማስጠበቅ አንፃር በትኩረት እየሠራ ነው ተብሏል።