ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የገቢዎች ሚኒስቴር በህዳር ወር 19.2 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ።
ይህ ከፍተኛ ገንዘብ የተሰበሰበው ከአገር ውስጥ ገቢ እና ወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ እንዲሁም ከሎተሪ ሽያጭ መሆኑ ታውቋል።
በተጨማሪም ሚኒስቴሩ ከሐምሌ እስከ ህዳር በነበሩት 5 ወራት ከ126 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ጠቁሞ
ይህም የእቅዴ 101 በመቶ እንደሆነ ገልጿል።
ገንዘቡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ደግሞ ከ17.4 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለው ተጠቅሷል።