በመቀለ የመንግሥት ሠራተኞች አሁንም ወደሥራ ገበታቸው አልተመለሱም ተባለ

በመቀለ የመንግሥት ሠራተኞች አሁንም ወደሥራ ገበታቸው አልተመለሱም ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በዶ/ር ሙሉ ነጋ የሚመራው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በመቀሌ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን በማስመልከት ውይይት አድርጊያለሁ አለ።

የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በመቀለ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ወደሥራ ገበታቸው ተመልሰዋል ብለው ቢዘግቡም፤ የተለያዮ ሚዲያዎች በበኩላቸው በዋና መዲናዋ የመንግሥት ሠራተኞች አሁንም በቤታቸው ለመቀመጥ መገደዳቸውንና ሥራ እንዳልተጀመረ ጠቁመዋል።
በመቀሌ ከተማ ተካሄደ በተባለው ውይይት ፤
ሠራተኞቹ የህግ ማስከበር ዘመቻው በተካሄደበት ወቅት ከአንድ ወር በላይ በቤታቸው መቆየታቸውን ጠቁመው፣
የመንግስት ሠራተኛ የህዝብ አገልጋይ እንጂ የፖለቲካ አራማጅ ስላልሆነ ወደ መደበኛ ሥራችን ለመመለስ ዝግጁ ነን ብለዋል።

LEAVE A REPLY