ወደሱዳን የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ለመመለስ መንግሥት እንቅስቃሴ ጀመረ

ወደሱዳን የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ለመመለስ መንግሥት እንቅስቃሴ ጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– መንግሥት ወደ ሱዳን የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ከሱዳን መንግሥት ጋር በመነጋገር ወደ ሀገር ለመመለስ እየሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

በትግራይ ክልል በነበረው አለመረጋገት እስካሁን 40 ሺህ ተፈናቃዮች ወደ ሱዳን መሰደዳቸውን ገልጸው፣ ወደ ሀገር ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን የተናገሩትየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ ከስደተኞቹ መካከል በወንጀል የተሳተፉና የሸሹ ስለሚኖሩ በዚህ ላይ መንግሥታቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
የቀይ መስቀልና ሌሎች የሰብኣዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ለስደተኞች ድጋፍ ማድረግ የሚችሉበት ሁኔታ እንደተመቻቸም የጠቆሙት ቃል አቀባዮ፤ በትግራይ ክልል የተለመደ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ እንደተጀመረ፣ በክልሉ የስልክ፣ የመብራትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች መስተካከላቸውን አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY