የህግ ማስከበር ዘመቻውን መንግሥት ብዙ ትምህርት እንደወሰደበት ሞፈሪያት ካሚል ተናገሩ

የህግ ማስከበር ዘመቻውን መንግሥት ብዙ ትምህርት እንደወሰደበት ሞፈሪያት ካሚል ተናገሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ክልል በትህነግ ላይ የተወሰደው የህግ የማስከበር ዘመቻ መንግሥት ብዙ ትምህርት የወሰደበት መሆኑን ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

ከመከላከያ ድጋፍ አሰባሳቢ የሚኒስትሮች ዐቢይ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን በጦር ኃይሎች ሪፈራል ሆስፒታል በመገኘት በህግ ማስከበር ዘመቻው ላይ የተካፈሉ የሠራዊቱን አባላት የጎበኙት የሰላም ሚኒስትሯ ሞፈሪያት ካሚል፤ “እኛ እዚህ የተገኘነው በአጥንታቸውና በደማቸው ስለ ሀገራቸውና ህዝባቸው ዋጋ የከፈሉ ወገኖቻችንን ባይመጥንም አክብሮታችንን እና አብሮነታችን ለመግለጽ ነው” ሲሉም ተደምጠዋል።
ሰሞኑን ድምጻቸው ጠፍቶ የከረመውና በስልጣናቸው ዙሪያ በርካታ አሉባልታዎች ሲናፈስባቸው የከረሙት ሞፈሪያት ካሚል የህግ ማስከበር ሥራው ጸረ ሰላም ኃይሎችን ከማስወገድ ባሻገር መንግሥት በቀጣይም እንዲህ አይነት ችግሮች ሲከሰቱ ምን ማድረግ እንዳለበት በቂ ትምህርት የወሰደበት እንደሆነም አብራርተዋል።

LEAVE A REPLY