63 በማዕድን ማምረት እና ምርምር ሥራ የተሰማሩ ተቋማት ተሰረዘ

63 በማዕድን ማምረት እና ምርምር ሥራ የተሰማሩ ተቋማት ተሰረዘ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በማዕድን ማምረት እና ምርምር ሥራ ላይ እንዲሰማሩ ፈቃድ ከተሰጣቸው 213 ተቋማት ውስጥ 63 የሚሆኑት ፈቃዳቸው ተሰረዘ።

 ፈቃዳቸው ከተሰረዘባቸው 63 ተቋማት ውስጥ 38 ተቋማት በማዕድን ምርት ላይ የተሰማሩ ሲሆን፣ 25ቱ ደግሞ በማዕድን ምርምር ላይ ተሰማርተው የነበሩ ናቸው።
ተቋማቱን ወደ መስመር ለማስገባት ብዙ ጥረት ተደርጓል ያሉት የነዳጅና የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ፤ የ
ፈቃዳቸው የተነጠቀባቸው የማዕድን ቦታዎች በአፋጣኝ ወደ ሥራ እንዲገቡና የማዕድን ሀብቶችን በተገቢው መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይደረጋል ብለዋል።
 4 ሺኅ 83.2 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቦ 299.1 ሚሊየን ዶላር ከውጭ ምንዛሪ፣ ከጌጣ ጌጥ ማዕድናት ደግሞ 3.8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ባለፉት አምስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ 302.9 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱም ታውቋል።

LEAVE A REPLY