በትግራይ 2.3 ሚሊዮን ሕጻናት ከሰብኣዊ አቅርቦት ውጪ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ገለጸ

በትግራይ 2.3 ሚሊዮን ሕጻናት ከሰብኣዊ አቅርቦት ውጪ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፉት ሳምንታት በትግራይ በተነሳው ጦርነት ምክንያት 2.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ህፃናት ከሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ውጪ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ይፋ አደረገ።

ለችግር ከተጋለጡት መሀል አብዛኞቹ ስደተኛና ሕጻናት በመሆናቸው፣ በአጠቃላይ ሕጻናትን መጠበቅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ሥራ ነው ያለው የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ዐቀፉ የሕጻናት መርጃ ድርጅት (ዮኒሴፍ) አስታውቋል።
ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሰብኣዊ እርዳታዎችን ለማድረስ ስምምነት ላይ ቢደርስም ድርጅቶቹ በክልሉ የእርዳታ አቅርቦት ለማድረስ እንዳልተቻለ ደጋግመው በመግለጽ ላይ ናቸው።
“ለሕጻናቱ የሚሰጠው እርዳታ አቅርቦት በዘገየ ቁጥር፣ ምግብ፣ በችጋር ለተጋለጡት ሕጻናትን ለማደስ የሚያስፈልጉ አልሚ ምግቦች፣ ህክምና፣ ውሃ፣ ነዳጅና እና ሌሎችም አስፈላጊ ነገሮች እያጠሩ ወደ ከፋ ሁኔታ ያመራሉ” ሲልም ስጋቱን አስቀምጧል።

LEAVE A REPLY