አንጋፋው የትያትር ባለሙያ ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዮ

አንጋፋው የትያትር ባለሙያ ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዮ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– አንጋፋው የቲያትር ባለሞያ  ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ በ84 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዮ።
በኪነ ጥበቡ ዘርፍ ትልቅ አሻራቸውን ያኖሩት ረ/ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ የቲያትር መምህር፣ ጸሐፊ ተውኔት፣ አዘጋጅ እና ተርጓሚ ሆነው ለጥበብ ፋይዳ ያላቸውን ሥራዎች ሠርተዋል።
ዕቃው፣ መተከዣ፣ መደበሪያ፣ የኦማር ካያም የግጥም ስብስብ ትርጉም ካበረከቷቸው መፅሐፍት ውስጥ የሚጠቀሱላቸው  ተስፋዬ ገሰሰ፤ የሼክስፒር ድርሰት የሆነው ሀምሌት ቲያትርን ጨምሮ በበርካታ ቲያትሮች ላይም በድርሰት፣ በትወና እና በአዘጋጅነት ተሳትፈዋል።
በሁለት ተከታታይ ክፍሎች ለእይታ የበቃው ሼፉ ፊልም ላይ  የተሳተፉት አንጋፋው የኪነ ጥበብ ሰው በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ የትያትር ዲፓርትመንት በመምህርነትና በዲንነት ለበርካታ አመታት አገልግለዋል።

LEAVE A REPLY