ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– አዲስ የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ በሚሊዮን የሚቆጠሩ በየመንና በአፍሪካ ቀንድ የሚኖሩ ሕዝቦችን ሕይወት ላይ አደጋ እንዲያንዣብብ ማድረጉ ተሰማ።
በምስራቅ ኢትዮጵያ እና ሶማልያ እንዲሁም ኬንያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ የተለያዮ ቦታዎች የአንበጣ መንጋን ለማራባት ምቹ ሁኔታ እየታየ ነው ያለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤ በቀይ ባሕር ሁለቱም አቅጣጫዎች እየተራባ የሚገኘው አንበጣ በኤርትራ፣ ሳዑዲ አረቢያና የመን ላይ አደጋ መደቀኑንም ከወዲሁ ጠቁሟል።
በምስራቅ አፍሪካ ባለፈው ዓመት ከ70 ዓመታት በላይ ያልታየ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ የተከሰተ ሲሆን በኢትዮጵያም የተለያዮ ስፍራዎች ይህ የአንበጣ መንጋ በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ አይዘነጋም።