የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በአዲስ አበባ ከሚኖሩ የትግራይ ወጣቶች ጋር ተወያየ

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በአዲስ አበባ ከሚኖሩ የትግራይ ወጣቶች ጋር ተወያየ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፈጠሩት የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አዲስ አበባ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ።

ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን በሀገር እና በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመውን ክህደት በማውገዝ መንግሥት የጀመረውን ሕግ የማስከበር ሥራ እና መልሶ ግንባታ ሀሳብን በመረዳት ሁሉም የክልሉ ወጣቶች ከመንግሥት ጎን እንዲሰለፉ በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በቀጣይ በተለያዮ የሀገሪቱ ክልሎች ከሚገኙ የትግራይ ነዋሪዎች ጋር ተመሳሳይ የውይይት መድረኮችን እንደሚያዘጋጅ ተነግሯል።

LEAVE A REPLY