የአማራ ልዮ ኃይል የወሰደው እርምጃ ትክክል እንደነበር አቶ ዛዲግ አብርሃ አረጋገጡ

የአማራ ልዮ ኃይል የወሰደው እርምጃ ትክክል እንደነበር አቶ ዛዲግ አብርሃ አረጋገጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ጁንታው የመጀመሪያውን ጥይት የተኮሰው በአማራ ሕዝብ ላይ በመሆኑ የአማራ ኃይል የወሰደው እርምጃ ራሱን የመከላከል መሆኑን አቶ ዛዲግ አብርሃ መሰከሩ።

በትግራይ ክልል የማንነት ጥያቄ ለሚያነሱት ለራያ እና ለወልቃይት ህዝቦች ኑሯቸው ሲዖል ነበር ያሉት የአቅም ግንባታ ሚኒስትሩ አቶ ዛዲግ አብርሃ፤  “ማይካድራ ወንጀል የሰሩ የጁንታው ቡድን ሱዳን አልተደበቁም ማለት አይቻልም። ሌላው ቀርቶ የትግራይ ልዩ ኃይሎች በጦርነቱ ሲቆስሉ፣ ዩኒፎርማቸውን በማውለቅ ሲቪል መስለው ነው” ሲሉ ከአሀዱ ቲቪና ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ ተናግረዋል።
“የአማራ ልዩ ሃይል በጁንታው ጥቃት ደርሶበታል፣ የአማራ ልዩ ሀይል ራሱን የመከላከል መብት አለው። የሕዝቦች ጥያቄ በሂደት ይመለሳል። በትግራይ ክልል መኖር አንፈልግም ብለዋል፤ እኔ የተወለድኩበት የራያ አካባቢ ጥያቄያቸውን በግልፅ አቅርበዋል። የማንነት ጥያቄ ያላቸው ህዝቦች አሸንፏል” በማለት አሁን ያለውን እንቅስቃሴ በግልጽ ያስቀመጡት ዛዲግ አብርሃ፤ ሁሉም ነገር በሂደት መፍትሄ ያገኛል ብለዋል።

LEAVE A REPLY