ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጃንሜዳ ታቦት ማደሪያን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አስረከቡ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጱዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስና የተለያዩ ሀገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት፣ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በጃንሜዳ የሚገኘውን የባሕረ ጥምቀቱን ስፍራ ጎብኝተዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ጃንሜዳን ለጥምቀት በዓል እንዲደርስ ቃል በገባው መሰረት እዚህ ደረጃ ደርሶ በማየታቸው መደሰታቸውን የገለጹት ብፁዕ አቡነ ማትያስ፤ ጃንሜዳ ለበዓሉ ማክበሪያ ዝግጁ ለማድረግ ላደረጉት የከተማ አስተዳደሩና በፅዳት ሥራ ለተሠማሩት የከተማ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።