ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ጁንታው በትግራይ ክልል ባሉ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ የህግ ታራሚዎችን ሰብስቦ በመቐለ ከተማ ውስጥ በመልቀቅ ዝርፊያ እንዲፈጸም አድርጓል ተባለ።
በመከላከያ ሠራዊት ጠንካራ እርምጃ መወሰዱን ተከትሎ የጁንታው አባላት በክልሉ የተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ በተለያዩ ወንጀሎች ተይዘው የእስር ጊዜያቸውን እየፈጸሙ የነበሩ ታራሚዎችን በመቐለ ከተማ ለቋቸዋል ያሉት የአዲሱ የትግራይ አስተዳደር የመቀለ ከንቲባ ናቸው።
በተለያዩ ወንጀሎች ተይዘው የነበሩ ሰዎችን በከተማዋ ውስጥ በመልቀቅ የግለሰቦችን ሱቅ ጭምር እንዲዘረፉ ተደርጓልም ያሉት ከንቲባው ይህን ተከትሎ ሕዝቡ ከፍተኛ ስጋት ላይ መውደቁን አስረድተዋል። በዘረፋው የተለያዮ የንግድ ተቋማት፣ ማዘጋጃ ቤት፣ ፍርድ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ሰነዶችን ጨምሮ በርካታ ሱቆች ተጠቂዎች ሆነዋል።