10 ዓለም ዐቀፍ ተመራማሪዎች የኮሮናን መነሻ ለማጥናት ቻይና ውሃን ሊያመሩ ነው

10 ዓለም ዐቀፍ ተመራማሪዎች የኮሮናን መነሻ ለማጥናት ቻይና ውሃን ሊያመሩ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መነሻ ለማጥናት ዐሥር ዓለም ዐቀፍ ተመራማሪዎችን የያዘ ቡድን በሚቀጥለው ወር ወደ ቻይና ዉሃን ያቀናል ተባለ።

የዓለም ጤና ድርጅት ምርምሩን የሚያካሂደው ለወቀሳ ሳይሆን ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኞችን ለመከላከል እንደሆነ የጠቆመው አሶሺየትድ ፕሬስ፤ ጉዞው በወረርሽኙ ጥፋተኛ የሆነውን ሀገር ለመፈለግ ሳይሆን፣ ምን እንደተከሰተ ለመረዳት መሞከር እና በእነዚያ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ወደፊት ሊከሰት የሚችለውን አደጋ መቀነስ እንደሚቻል ለመገምገም መሆኑ ታውቋል።
ከዚህ ባሻገር ቫይረሱ መቼ መዛመት እንደጀመረ እና መነሻው ዉሃን ይሁን አይሁን ለማወቅ እንዲቻል ጥረት ይደረጋል ያለው የዓለም ጤና ድርጅት፤ ምርምሩ ከአራት እስከ አምስት ሳምንታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልጿል።

LEAVE A REPLY