ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የሕዝብ ንባብ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ገለጸ።
በሕዝብ ንባብ ቤቱ ከአሁን ቀደም በአንድ ጊዜ ከ1000 በላይ አንባቢዎችን ያስተናግድ እንደነበር የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ዳይሬክተሩ አቶ ያሬድ ተፈራ ፤ አሁን ግን ከግማሽ በላይ በመቀነስ 326 ሰዎች እንደሚስተናገዱ ተናግረዋል።
ተቋሙ ሥራ መጀመሩን ተከትሎ አንባቢዎች የተጠቀሙባቸው መጻሕፍትም ከ3 እስከ 5 ቀናት ከንክኪ ርቀው ተለይተው እንዲቆዮ ይደረጋል ነው የተባለው። ይህን ለማከናወንም አንድ ክፍል ማዘጋጀቱን ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ አስታውቋል።
ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የንባብ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል የተባለው ቤተ መጻሕፍቱ፤ ለአጥኚዎችና ተመራማሪዎች ከነሐሴ 15፣ 2012 ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሷል።