መንግስት ጁንታው የሚላቸውን የትህነግ አመራሮችን ለጠቆመ 10 ሚሊዮን ብር ይሰጣል ተባለ

መንግስት ጁንታው የሚላቸውን የትህነግ አመራሮችን ለጠቆመ 10 ሚሊዮን ብር ይሰጣል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የህወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ 10 ሚሊዮን ብር የማበረታቻ ሽልማት መዘጋጀቱን የመከላከያ ሠራዊት ገለጸ።

የጁንታውን ቡድን አጋልጦ ለሚሰጥ ማንኛውም ዜጋ የማበረታቻ ሽልማት ተዘጋጅቷል ያሉት በመከላከያ ሠራዊት የሕብረት መረጃ ዋና መምሪያ ሓላፊ ሌ/ጀነራል አስራት ዴኔሮ፤ የህወሓት ቡድንን ለመያዝ በሚደረገው ዘመቻ የትግራይ ሕዝብን ጨምሮ ሁሉም ዜጋ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል።
የጥፋት ቡድኑን ለማጋለጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ፤ ለኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ ለፌዴራል ፓሊስ እና ለደህንነት አካላቶች መረጃዎችን መስጠት ይችላሉ ተብሏል።

LEAVE A REPLY