አዲግራትና ውቅሮ ከተሞች የኤሌክትሪክ አቅርቦት አገኙ

አዲግራትና ውቅሮ ከተሞች የኤሌክትሪክ አቅርቦት አገኙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ክልል ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በወደሙ መሠረተ ልማቶች ሳቢያ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አቅርቦት በአዲግራትና ውቅሮ ከተማ መጀመሩ ተሰማ።

የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቴክኒክ ባለሞያዎች ጉዳት የደረሰባቸውን የዝቅተኛና መካከለኛ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ላይ ባደረጉት የጥገናና መልሶ ግንባታ ሥራ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የቴክኒክ ባለሞያዎች በከፍተኛ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ላይ ባደረጉት ጥገና በሁለቱ ከተሞች ዳግም አገልግሎት መስጠት ተጀምሯል።
በሌሎች የትግራይ ከተሞችም የተቋረጡ የመሠረተ ልማት አገልግሎቶችን ለማስቀጠል በፌደራል መንግሥቱና በአዲሱ የትግራይ ክልል አስተዳደር አማካይነት እየተካሄደ ነው ተብሏል።

LEAVE A REPLY