ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ ፈንድ በኢትዮጵያ ለሰብኣዊ ድጋፍ የሚውል ከ35 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ አደረገ።
የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል ህግ በማስከበር ሂደት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ እንዲችል ነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 35 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ የሰጠው።
የገንዘብ ድጋፉ በተለይ በትግራይ ክልል አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ለንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የንጽህና መጠበቂያና የሕክምና ቁሳቁስ አቅርቦት ይውላል መባሉን ሰምተናል።