ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአውሮፓ ሕብረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሦስት ሀገራት የ23 ነጥብ 3 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን አድርጊያለሁ አለ።
በሕብረቱ መግለጫ መሠረት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኬንያና ሱዳን የእርዳታው ተቋዳሽ ሆነዋል።
ከ23 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ውስጥ 18 ነጥብ 8 ሚሊየን ዩሮው በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚውል ሲሆን፣ ሁለት ሚሊየን ዩሮው ደግሞ ለሱዳን የተደረገ ድጋፍ ነው ተብሏል።
ቀሪው 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ዮሮ የሚሆነው ገንዘብ በኬንያ የምግብ ዋስትና ለተጋረጠው አደጋ የሚውል ነው። የአውሮፓ ሕብረት በፈረንጆቹ 2020 ለኢትዮጵያ ያደረገው ድጋፍ 63 ነጥብ 2 ሚሊየን ዩሮ መድረሱን አስታውቋል።