ኮ/ል ብርሃኑ ባየህና ጀነራል አዲስ ተድላ ከ30 ዓመት ጥገኝነት በኋላ ሰኞ ከጣልያን...

ኮ/ል ብርሃኑ ባየህና ጀነራል አዲስ ተድላ ከ30 ዓመት ጥገኝነት በኋላ ሰኞ ከጣልያን ኤምባሲ ይወጣሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ 30 ዓመታት በጥገኝነት የሚገኙት ሁለት የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሰሞኑን በይቅርታ ሊወጡ ይችላል ተባለ።

ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና ሌፍተናንት ጀነራል አዲስ ተድላ ከደርግ መንግሥት መውደቅ በኋላ (ግንቦት 19 ነው የገቡት) በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ጥገኝነት በመጠየቅ ለሦስት ዐሥርት ዓመታት ለመቆየት መገደዳቸው አይዘነጋም።
በወቅቱ በኤምባሲው ጥገኝነት ከጠየቁት አራት የደርግ ባለሥልጣናት መካከል ሁለቱ በሕይወት ባይኖሩም፤ በደርግ ዘመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ብርሃኑ ባየህ እና  የሠራዊቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል አዲስ ተደላ በቀጣዮቹ ቀናት በሚሰጣቸው ይቅርታ ከመጠለያቸው ሊወጡ ይችላሉ።
 የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለቱ የቀድሞ ባለስልጣናት፤ የሞት ፍርዳቸው ወደ እድሜ ልክ እስራት በርዕሰ ብሔሯ የተቀነሰላቸው ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የፊታችን ሰኞ ለሠላሣ ዓመት ከቆዮበት ኤምባሲ በይቅርታ እንዲወጡ እንደሚደረግ የተለያዮ ምንጮች እየጠቆሙ ናቸው።

LEAVE A REPLY