የትግራይ ሕዝብ የትህነግ አባላትን አሳልፎ ለመንግሥት እንዲሰጥ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ጠየቁ

የትግራይ ሕዝብ የትህነግ አባላትን አሳልፎ ለመንግሥት እንዲሰጥ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ጠየቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና የትግራይ ሕዝብ ለራሱ ሰላምና ደሕንነት ሲል የጁንታውን ርዝራዦች አሳልፎ ሊሰጥ እንደሚገባ  ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ተናገሩ።

የመጀመሪያው የህወሓት መሥራችና የድርጅቱ የቀድሞ ሊቀመንበር የነበሩት አረጋዊ፤ ህወሓት ከማንም በላይ ሲጨቁነውና ሲዘርፈው የኖረው የትግራይ ሕዝብን እንደሆነ አስታውሰዋል።
በትግራይ ክልል የነበሩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህገ መንግሥቱ በሚፈቅድላቸው መንገድ በክልሉ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ ጽንፈኛው የትህነግ ቡድን አፈና ሲያደርግባቸው መቆየቱን የገለጹት አንጋፋው ፖለቲከኛ፤  አሁን ላይ ግን በክልሉ ምቹ መደላድል ይፈጠራል የሚል እምነት አለኝ ብለዋል።
በዚህ ወቅት ከሠላሣ ዓመት በኋላ የነፃነት አየር መተንፈስ የጀመረው የትግራይ ሕዝብ ይህ ሰላሙ እንዲዘልቅ የሚፈልግ ከሆነ በመንግሥት በኩል የቀረበውን ጥሪ በመቀበል የጁንታውን አባላት ለመንግሥት አሳልፎ መስጠት እንዳለበት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY