28 አትሌቶችና አሰልጣኞችን የያዘው መኪና ሰበታ ላይ መንገድ ስቶ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ

28 አትሌቶችና አሰልጣኞችን የያዘው መኪና ሰበታ ላይ መንገድ ስቶ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ

TO GO WITH AFP STORY BY JENNY VAUGHAN Two athletes run at the training grouns of Ethiopia's long distance and marathon runner Kenenisa Bekele in Sululta near Addis Ababa on January 16, 2014. Bekele already holds two world records, and now he says he is eyeing a third -- this time in the marathon. The running will be the star draw of the April 6 Paris marathon, just a week before track rival Mo Farah of Great Britain makes his own marathon debut in London -- making for two back-to-back must-watch performances. AFP PHOTO/CARL DE SOUZA (Photo credit should read CARL DE SOUZA/AFP via Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ትናንት ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1ሰዐት ላይ የመብራት ሀይል አትሌቶችን የያዘ መኪና መንገድ ስቶ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተሰማ።

ነገ እሁድ በሱሉልታ የሚደረገውን  የሀገር አቋራጭ የውድድር ቦታ ለመጎብኘትና በዚያውም ልምምድ ለማድረግ አትሌቶቹ እየተጓዙ ባለበት ሁኔታ፤ 10 ኪ ሜ ላይ መኪናው መንገድ ስቶ አትሌቶችና አሰልጣኞች በጠቅላላ 28 ሰው የሚሆኑ ስፓርተኞችን እንደያዘ  መገልበጡን ለክለቡ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለኢትዮጵያ ነገ ገልጸዋል።
ባልታሰበው የመኪና አደጋ የሞተ ሰው ባይኖርም  አምስት  አትሌቶችና እና አንድ አሰልጣኝ ተጎድተው፤  ዳኑ የአጥንት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል  እንዲገቡ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY