ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ወደ ዮንቨርስቲ ሕይወት የሚቀላቀሉ አዲስ ገቢ የዩንቨርሲቲ ሴት ተማሪዎችን ለማብቃት ያስችላል የተባለ መርሀግብርን ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ አስጀመሩ።
ስርዓተ ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ መንግሥት እየሠራ ይገኛል ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ ከዚህ ባሻገር ሴቶችን በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚነታቸውን የማረጋገጥና ወደ አመራር ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት በመድገረግ ላይ ነው ብለዋል።
በመርሀ ግብሩ የዩንቨርሲቲ አዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎችን ስኬታማ ከሆኑ ሴቶች ጋር በማጣመር ለሀገር የሚጠቅሙ ሴቶችን ለማብቃት፣ በተመደቡበት ዩንቨርሲቲ የሚገጥሙአቸዉን ችግሮች በመጋራትና በማገዝ ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።