ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ ከተባሉት 85 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል 26ቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰረዘ።
በብሔርና በሀገር ዐቀፍ ፓርቲነት በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ከሚገኙት ውስጥ በፓርቲነት ለመቀጠል የሚያስችላቸውን መስፈርቶች ሳያሟሉ የቀሩት 26 የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረዛቸውን ተከትሎ አሁን ላይ በሀገሪቱ ሕጋዊ እውቅና ያላቸው ፓርቲዎች 59 ሆነዋል።
በምርጫ ቦርድ ከተሰረዙት መካከልም የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የመላው ኢትዮጵያዊያን ብሔራዊ ንቅናቄ (መኢብን)፣ የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ)፣ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ግንባር ቀደሞች ሆነዋል።
ከእነዚህ ድርጅቶች በተጨማሪ በተለያዩ ምክንያቶች ማብራሪያ እንዲሰጡ ወይም የሚጠበቅባቸውን አሟልተው እንዲያቀርቡ የተወሰነ፣ እንዲሁም የማጣራት ሂደታቸው ያልተጠናቀቀ ፓርቲዎች ከመኖራቸው ጋር ተያይዞ የሚሰረዙት ፓርቲዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ተብሏል።