በመተከል ዞን የተገደሉት ንጹሐን ዜጎች ቁጥር 120 ደርሷል ተባለ

በመተከል ዞን የተገደሉት ንጹሐን ዜጎች ቁጥር 120 ደርሷል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ትናንት ሌሊት (ሊነጋጋ ሲል) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አረጋገጠ።

ግድያው ዘግናኝና አስከፊ ነበር ያለው ዓለም ዐቀፉ የሰብኣዊ መብት ተሟጋች  አምንስቲ ኢንተርናሽናልም በተመሳሳይ በጥቃቱ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ንጹሃን ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል ብሏል።
በጥቃቱ አካባቢ የነበሩ የዓይን እማኞችንና በአካባቢው በሚገኝ ሆስፒታል የሚሠሩ የጤና ባለሙያዎችን ዋቢ ያደረገው ቢቢሲ ደግሞ  120 ሰዎች እንደተገደሉና ሌሎች በርካቶ ዜጎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ዘግቧል።
“እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል። በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር በእጅጉ አዝኛለሁ” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ሀዘናቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ መንግሥት ችግሩን ከሥሩ ለመፍታት ስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ ማድረጉን አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY