ዶ/ር አረጋዊ በርሄና አቶ የሺዋስ አሰፋ የኢቢሲ የቦርድ አባል እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ...

ዶ/ር አረጋዊ በርሄና አቶ የሺዋስ አሰፋ የኢቢሲ የቦርድ አባል እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመረጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ከጠዋቱ ሦስት ሰዐት አካባቢ እስከ 5 ሰዐት ድረስ በዝግ መወያየቱ ተሰምቷል።

ጋዜጠኞቾ እንዳይገቡ በተከለከለበት 2 ሰዐት በወሰደው የውይይት ጊዜ የብሔር ማንነትን መሰረት አድርጎ እየተፈፀመ ያለው ግድያ እየተባባሰ ስለሄደበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉዳይ እንደሆነ ከምክር ቤት አባላት ያገኘውን ጥቆማ ዋቢ በማድረግ ሸገር ራዲዮ ዘግቧል።
የተለያዮ አጀንዳዎች በተነሱበት የዛሬው ስብሰባ በቀዳሚነት ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 3 አዳዲስ የቦርድ አባላት ሹመት ላይ ውይይት አድርጓል።
 በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እጩ ሆነው የቀረቡት ዶ/ር አለሙ ስሜ የኢቢሲ የቦርድ ሰብሳቢ፣ ዶ/ር አረጋዊ በርሄና አቶ የሸዋስ አሰፋ ደግሞ የቦርድ አባል ሆነው ሹመታቸው እንደፀደቀላቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY