ሥድሥተኛው ሀገራዊ ምርጫ ግንቦት 28 እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

ሥድሥተኛው ሀገራዊ ምርጫ ግንቦት 28 እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በዚህ ዓመት የሚካሄደው ሀገራዊና ክልላዊ አጠቃላይ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ዛሬ በምርጫ ቦርድ ይፋ ተደረገ።

የትግራይ ክልልን ያላካተተው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ሥድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28/2013 ዓ.ም ሆኗል። የአዲስ አበባ ከተማና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር የድምጽ መስጫ ቀን ከአንድ ሳምንት በኋላ ሰኔ 5/2013 ዓ.ም መሆኑ ታውቋል።
የወጣው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ የትግራይ ክልልን የማይጨምር መሆኑ ነው ያለው ምርጫ ቦርድ፤ በክልሉ የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለምርጫ በሚስማማ መልኩ ሲመቻች፣ ለክልሉ የምርጫ ሰሌዳ እንደሚዘጋጅም ገልጿል።
ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ውጪ ድምጽ በሚሰጥበት ዕለት በተደራቢነት የደቡብ ምዕራብ ሕዝበ ውሳኔ እንደሚሰጥም ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ሕዝበ ውሳኔው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በአዲስ መልክ ከማዋቀር ጋር ተያያዞ የሚካሄድ መሆኑም ተሰምቷል።
ቀደም ብለው ከሚካሄዱ የምርጫ ዝግጅቶች በተጨማሪ የዕጩዎች ምዝገባ ከየካቲት 8  እስከ 21 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ፣ በምርጫው የሚወዳደሩ እጩዎች የምረጡኝ ዘመቻቸውን ከየካቲት 08 2013 እስከ 23 2013 ቀን ድረስ ለአስራ አምስት ቀን እንደሚያካሂዱ ነው የተገለጸው።

LEAVE A REPLY