በትግራይ ክልል ለሰብኣዊ ድጋፍ የሚውል 6ሚሊዮን ዶላር የስዊዲን መንግሥት ሰጠ

በትግራይ ክልል ለሰብኣዊ ድጋፍ የሚውል 6ሚሊዮን ዶላር የስዊዲን መንግሥት ሰጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የስዊድን መንግሥት ከፍተኛ የሆነ መፈናቀልና የሰላም እጦት ላለበት ትግራይ ክልል ለሰብኣዊ ድጋፍ የሚውል 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረገ።

ይህ ድጋፍ በትግራይ ክልል በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ለተጎዱ ዜጎች የሚሰጥ ሲሆን፤ እርዳታው በዓለም ዐቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ በዓለም የምግብ ፕሮግራም እና በዓለም ዐቀፉ የስደተኞች ተቋም አማካኝነት ለተጎጂዎች የሚደርስ ነው ተብሏል።
በትግራይ ክልል በርካታ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ተከትሎ የተለያዮ ሀገራትና ዓለም ዐቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች እርዳታ በመለገስ ላይ ናቸው።

LEAVE A REPLY