በኮንሶ ዞን ሥድሣ ሰዎች መገደላቸውንና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸው ተረጋገጠ

በኮንሶ ዞን ሥድሣ ሰዎች መገደላቸውንና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸው ተረጋገጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኮንሶ ዞን ባለፈው ኅዳር ወር መጀመሪያ ላይ በተደጋጋሚ በተከሰቱ ግጭቶች ከሥድሣ በላይ ሰዎች እንደተገደሉና  በርካቶች ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ።

በዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ግጭቶቹን በተመለከተ ባደረገው ማጣራት መሠረት ቢያንስ 66 ሰዎች ተገድለው፣ 39 ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ በርካታ ቤቶችና ንብረቶች በእሳት ተቃጥለው መውደማቸው ተረጋግጧል።
በአካባቢው ባጋጠሙት ግጭቶች ሳቢያ ከ130 ሺኅ በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ያለው የኮሚሽኑ ሪፖርት፤ በጥቃት ፈጻሚዎቹ በጭካኔና በአሰቃቂ ሁኔታ ሰዎች በግፍ ከመገደላቸው ባሻገር የተሰበሰበ እህልን ጨምሮ ንብረት እና የእርሻ ቦታዎች መሉ በሙሉና በከፊል በእሳት ወድመዋል ሲል ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY