የጭካኔ ተግባር በፈጸሙት ታጣቂዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ ደመቀ መኮንን አስታወቁ

የጭካኔ ተግባር በፈጸሙት ታጣቂዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ ደመቀ መኮንን አስታወቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በዜጎች ላይ ጭካኔ በተሞላበት ጥቃት እየፈጸሙ ባሉ ወንጀለኞች ላይ መንግሥት ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እየተፈጸመ ነው ያሉት ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ይህ የወንጀለኞች ተግባር እንዲቆም መንግሥት ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል ሲሉ ተደምጠዋል።
“ይሄ ችግር ወደ የት እያመራ እንደሆነ ሁሉም ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል” በማለት የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዜጎችን እየጨፈጨፉ ባሉ ወንጀለኞች ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ፣ ድርጊቱን ለማስቆም እና ወንጀለኞችን ለማደን በሚደረገው ጥረት የሁሉም ኅብረተሰብ ትብብር  አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY