ጀነራል ብርሃኑ ጁላና ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ከሪፐብሊካን ጦር ጋር መተከል ዞን ገቡ

ጀነራል ብርሃኑ ጁላና ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ከሪፐብሊካን ጦር ጋር መተከል ዞን ገቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በመተከል ዞን በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ዘግናኝ ጥቃት ተከትሎ ዛሬ ታህሳስ 16/2013 ጧት የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹሙ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ እና ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ግልገል በለስ (መተከል)  መግባታቸው ተሰማ።

መንግሥት በጉዳዮ ላይ ጠንካራ አቋም መያዙን ተከትሎ መከላከያ ሠራዊቱ በሚወስደው እርምጃ ዙሪያ ጥብቅ መመሪያዎች ለመስጠት ሁለቱ ጀነራሎች መተከል መገኘታቸውን የጠቆሙ ታማኝ ምንጮች፤ በከተማዋ ያሉ መሥሪያ ቤቶች በሙሉ መዘጋታቸውን፣ ዌስት ስታር ሆቴል በባለ ቀይ ለባሽ መለዮ ወታደሮች (ሪፐብሊካን ጦር) መጥለቅለቁንና ከተማዋም ፀጥ ረጭ ማለቷን ገልጸውልናል።
አፈትላኪ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ የክልሉ ፕሬዝዳንት አሻድሊ፣ የመተከል ዞን አስተዳዳሪ አትንኩት ሽቴ እና የኮማንድ ፖስቱ መሪ ኮሎኔል አያሌው በቁጥጥር ስር ሊውሉ ይችላሉ እየተባለ ነው።
የቤኒሻንጉል ክልል ፕሬዝዳንት የህነው የአሻድሊ ጠባቂዎች በመከላከያ ትዕዛዝ እንደተበተኑ፣ አሻድሊ በቁም እስር ላይ መሆኑ የገለጹ ምንጮቻችን፤ ዋነኛው የአትንኩት ሽቴ ጠባቂ ትናንት እንደታሰረ አረጋግጠዋል።

LEAVE A REPLY