የምርጫ ፀጥታ ግብረ ኃይል መቋቋሙን ወ/ት ብርቱኳን ሚዴቅሳ አስታወቁ

የምርጫ ፀጥታ ግብረ ኃይል መቋቋሙን ወ/ት ብርቱኳን ሚዴቅሳ አስታወቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በተዘጋጀው ሀገር ዐቀፍ የምርጫ ፀጥታ ዕቅድ ላይ የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ አካላት መወያየታቸው ተሰማ።

ውይይቱ ዕቅዱ በግንቦት ወር መጨረሻ የሚካሄደውን አገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ፣ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ለማስቻል ነው ተብሏል።
የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳና የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀነዓ ያደታ በሚመሩት የምርጫ ፀጥታ ዕቅድ የምክክር መድረክ የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ ተሳታፊ ሆነዋል።
ኢትዮጵያ በ2013 ዓ.ም ለምታካሂደው አገር ዐቀፍ ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ፀጥታ ግብረ ኃይል መቋቋሙን ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY