የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ

 ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ አቶ ሺሠማ ገብረ ሥላሤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት አስረክበዋል ።
ከከተማ አስተዳደሩ የተበረከተው ድጋፍ በክልሉ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ምላሽ ለመጠት እየተሠራ ላለው ሥራ አጋዥ ነው ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዚህ ቀደም የህግ የማስከበር የህልውና ዘመቻ አስተዋፅዖ ላደረጉ የአማራ እና የአፋር የፀጥታ ሀይሎች፣ እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎችን ለመደጎም ለእያንዳንዳቸው 3ሺኅ ኩንታል የምግብ እህል ድጋፍ ማድረጉ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY