የኮንሶና አሌ ሕዝቦችን ለማስታረቅ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው

የኮንሶና አሌ ሕዝቦችን ለማስታረቅ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው

 ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኮንሶ እና በአሌ ሕዝቦች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት ያስችላል የተባለ የእርቀ ሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ።

ሁለቱ ሕዝቦች ለረጅም ዘመናት የዘለቀ አብሮነታቸውን በማስቀጠል እርስ በርስ እንደ አንድ የቤተሰብ አባል ሆነው የዘለቀ ቢሆንም፤ አንዳንድ አካላት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የግል ጥቅም እና ፍላጎታቸውን መሠረት በማድረግ የፀጥታ ችግር ተከስቷል ነው የተባለው።
የኮንሶ እና  አሌ ሕዝቦችን ሰላም ለማስቀጠል በየአካባቢያቸው ወግና ባህል መሠረት እርቀ ሰላም አውርደው፣ የመተሳሰብ እና የመደጋገፍ ባህላቸውን ለማስቀጠል የእርቀ ሰላም ኮንፈረንስ ሲካሄድ የተለያዮ የክልልና የዞን አመራሮች መገኘታቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY